የ ዘወልድ ባህላዊ የእርቅ ስነ-ስርዓት

Authors

Abstract

በራያ ቆቦ ‹ሰንየ ሰገድ›፣ ‹ክፍሎ›፣ ‹መዘርድ› እና ‹ዘወልድ› በሚባሉ አራት ወንድማማቾች ስም የሚጠራ የሽምግልና ሥርዓት (የወንዝ አባቶች) እንዳለ ይነገራል። እያንዳንዳንዱ የሽምግልና ሥርዓት የሚከወንበት የራሱ አካባቢ አለው፤ ለዛሬው ከአራቱ የሽምግልና ሥርዓቶች ከቆቦ ዙሪያ እስከ መቅደላ ዞብል ድረስ ባለው አካባቢ የሚከናወነውን ‹ዘወልድ› የተባለውን ባህላዊ የሽምግልናና የእርቅ ሥርዓት እናስቃኛችሁ። ዘወልድ ባህላዊ የሽምግልናና እርቅ ሥርዓት መጠሪያውን ያገኘው ለረጅም ዘመናት በኅብረተሰቡ መካከል የሚፈጠሩ ማንኛውንም ግጭቶች በመፍታት ይታወቁ ከነበሩት ከላስታ አካባቢ ነዋሪ ‹ዘወልድ› ከሚባሉ ታላቅ አባት እንደሆነ ይነገራል። ዘወልድ ስያሜውን ካገኘበት አንስቶ ከትውልድ ትውልድ ተላልፎ ዛሬም ድረስ ማኅበራዊ የሠላም ማስጠበቂያ ሆኖ እያለገለ ይገኛል፡፡ ዘወልድ ዋና እና ምክትል ሊቀ መንበር፣ ዋና ጸሐፊ፣ ገንዘብ ያዥ፣ ቁጥጥር እና ሁለት አባላትን ያሉት አደረጃጀት ነው፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

Downloads

Published

2026-04-16

Issue

Section

Articles

How to Cite

የ ዘወልድ ባህላዊ የእርቅ ስነ-ስርዓት. (2026). Lalibela Journal of Social Science and Humanities, 1(1), 19-20. https://journals.wldu.edu.et/index.php/ljssh/article/view/3